የሹዋሊድ በዓል በዓለም ቅርስነት መመዝገቡ ለቱሪስት ፍሰት መጨመር የጎላ ሚና አለው - ኢዜአ አማርኛ
የሹዋሊድ በዓል በዓለም ቅርስነት መመዝገቡ ለቱሪስት ፍሰት መጨመር የጎላ ሚና አለው
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 11/2018 (ኢዜአ)፡- የሹዋሊድ በዓል በዓለም የማይዳሰስ ቅርስነት መመዝገቡ የቱሪስት ፍሰቱን በመጨመር ለሀገር ገፅታ ግንባታ የጎላ ፋይዳ አለው ሲሉ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ።
የሐረሪ ብሔረሰብ በየዓመቱ የሚያከብረው ባህላዊው የሸዋል ኢድ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ ተከብራል።
በዚሁ ወቅት ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን እንዳሉት፤ የሸዋል ኢድ በዓል የማኅበራዊ እሴቶቻችንን በማጎልበት አንድነት ይበልጥ እንዲጎለብት ከማስቻሉም ባሻገር በሐረሪ ክልል ያሉ የቱሪዝም ፀጋዎችን በማስተዋወቅ የብዝኃ ዘርፍ ኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ያስችላል።
የሹዋሊድ በተለይም የክልሉ ብሎም የሀገሪቱ የቱሪዝም ዘርፍ እንዲጎለብት ከማድረግ አንፃር የላቀ ጠቀሜታ እንዳለውም ጠቁመዋል።
ክልሉ በቱሪዝም ዘርፉ ያለውን እምቅ ዐቅም በመጠቀምም የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሠራ መሆኑን አስታውቀዋል።
የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) በሕዳር ቀር 2016 ዓ.ም በቦትስዋና በተካሄደው ስብሰባ የሸዋል ኢድ በዓል አከባበርን በማይዳሰስ የሰው ልጅ ቅርስነት መመዝገቡ ይታወሳል።