ቀጥታ፡

የመዲናዋ የስፖርት መሰረተ ልማቶች ዓለም አቀፍ ውድድሮችን የማስተናገድ ደረጃ ላይ መድረሳችንን ያሳያሉ-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ሚያዚያ 11/ 2018 (ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡ የስፖርት መሰረተ ልማቶች ዓለም አቀፍ ስፖርታዊ ውድድሮችን የማስተናገድ ደረጃ ላይ መድረሳችንን የሚያሳዩ ናቸው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡

ከንቲባ አዳነች በአዲስ አበባ የተገነቡ ዘመናዊ የስፖርት መሠረተ ልማቶች ውጤት ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ ዘርፍ ያላትን ታላቅ ዝና ዳግም ለማረጋገጥ እድል የሰጠ ነው ብለዋል፡፡


 

የተገነቡት የስፖርት መሰረተ ልማቶች መዲናችን ማንኛውንም ዓይነት ዓለም አቀፍ ውድድር የማስተናገድ ብቃትና ደረጃ ላይ መድረሷን የሚያሳዩ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በአዲስ አበባ የሚከናወኑ ውድድሮች ተተኪ አትሌቶችን ከማነቃቃት ባለፈ ለስፖርት ቱሪዝም ዕድገት የጎላ ፋይዳ እንዳላቸው አስረድተዋል፡፡


 

ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ምቹና ሳቢ ከማድረግ ባሻገር ለዓለም አቀፍ ኩነቶች የስበት ማዕከል መሆኗን በተግባር ማሳየት ተችሏል ነው ያሉት ከንቲባዋ፡፡

ዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ መድረኮችን ማዘጋጀት ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለውም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም