አርባምንጭ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ነጥብ ተጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
አርባምንጭ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ ፤ ሚያዝያ 11/2018 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንት አርባምንጭ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና አንድ አቻ ተለያይተዋል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቢንያም ጌታቸው በ16ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ግብ ኢትዮጵያ ቡና መሪ ሆኗል።
ከእረፍት መልስ ይድነቃቸው ያሲን በ67ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ጎል ለአርባምንጭ ከተማ አንድ ነጥብ አስገኝቷል።
ውጤቱን ተከትሎ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው ኢትዮጵያ ቡና በ38 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።
አርባምንጭ ከተማ በ24 ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃን ይዟል።
ሁለቱ ቡድኖች በተመሳሳይ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች አላሸነፉም።