ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሀሮ ደንዲ ሎጅን በይፋ መረቁ

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 11/2018 (ኢዜአ)፡-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የገበታ ለትውልድ መርሃግብር አካል የሆነውን የሀሮ ደንዲ ሎጅን ዛሬ በይፋ መርቀዋል፡፡


 

የደንዲ ሐይቅን ቁልቁል የሚመለከተው የሥነ-ምህዳር ቱሪዝም ልማት፣ ኢትዮጵያ ለከፍተኛ እና ዘላቂ የቱሪዝም ዘርፍ ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

‎ይህ ስኬት ኢትዮጵያ ያለመችውን ዳር እንደምታደርስ ህያው ምስክር ነው ሲልም ገልጿል፡፡


 

‎ሀገራችን ተፈጥሯዊ ውበቷን ካልተቆጠበ ጥረት ጋር በማቀናጀት፣ የራሷን መጻኢ ዕድል በራሷ የመገንባት ዐቅም እንዳላት በድጋሚ በተግባር ያረጋገጠችበት ስኬት መሆኑንም ጽህፈት ቤቱ አመላክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም