ቀጥታ፡

የሐይቅ እስጢፋኖስ የቅርስና የልማት ሥራዎች አርአያነት ያለው ነው-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2018 (ኢዜአ)፡- የሐይቅ እስጢፋኖስ የቅርስና የልማት ሥራዎች አርአያነት ያለው መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ታሪካዊ የሆነውን የሐይቅ አስጢፋኖስ ገዳም መጎብኘታቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ጠቁመዋል።


 

ከ800 ዓመታት በላይ ካስቆጠሩት ቅርሶች ሙዝየም በተጨማሪ፤ ገዳሙ በፍራፍሬ እና ቡና ልማት፣ በዶሮ እርባታ፣ በጥበበ ዕድ እና በዘይት ምርት የሚያከናውነው ተግባር እጅግ አስደናቂ ነው ብለዋል።

የሃይማኖት ተቋማት ለማኅበረሰቡ መንፈሳዊ ብቻ ሳይሆን፤ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት የሐይቅ እስጢፋኖስን መንገድ መከተል እንዳለባቸው ገልጸዋል።

#Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም