የሐዋሳ ከተማ የኮሪደር ልማት የማኅበራዊ ትሥሥር መሰረት እየሆነ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የሐዋሳ ከተማ የኮሪደር ልማት የማኅበራዊ ትሥሥር መሰረት እየሆነ ነው
ሐዋሳ፤ ሚያዝያ 11/2018 (ኢዜአ)፡- የሐዋሳ ከተማ የኮሪደር ልማት የተፈጥሮ ፀጋዋን ከማጉላቱ ባለፈ የማኅበራዊ ትሥሥር መሰረት መሆኑን የከተማዋ ከንቲባ ጥራቱ በየነ ገለፁ።
የሐዋሳ ከተማ 2ኛና 3ኛ ዙር የኮሪደር ልማት ሥራ ማጠናቀቂያ እና የ4ኛ ዙር የኮሪደርና የሐይቅ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር ተካሂዷል።
በዚሁ ወቅት ከንቲባው እንዳሉት፤ የሐዋሳን የቱሪዝምና ኮንፈረንስ ማዕከልነት ለማጠናከር ሥራዎች በተሻለ ፍጥነትና ጥራት መከናወናቸው ይቀጥላል።
የከተማዋ የኮሪደር ልማት ያላትን የተፈጥሮ ፀጋ አጉልቶ ከማውጣቱ በተጨማሪ፤ የቱሪዝም መስኅብና የማኅበራዊ ትሥሥር መሠረት እየሆነ ነው ብለዋል።
የግንባታ ሥራው ተጠናቆ ለአገልግሎት የበቃው የኮሪደር ልማት ሥራ የከተማዋን ውበትና የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት ያረጋገጠ መሆኑንም አንስተዋል።
4ኛው ዙር የኮሪደር ልማት 3 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር እንደሚሸፍን ጠቁመው፤ የሐይቅ ዳርቻ ልማቱም የሐዋሳ ሐይቅ ዳርቻን ይዞ እንደሚለማ አመላክተዋል።