ቀጥታ፡

የበቆሎ መስኖ ሥራችን ከፍ ባለ ስኬት ላይ ይገኛል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2018 (ኢዜአ)፡- ትኩረት ሰጥተን እየሠራንባቸው ከሚገኙት ምርቶች አንዱ የሆነው የበቆሎ መስኖ ሥራችን ከፍ ባለ ስኬት ላይ ይገኛል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ እንደ ሀገር ትኩረት ሰጥተን እየሠራንባቸው ከሚገኙት ምርቶች አንዱ የሆነው የበቆሎ መስኖ ሥራችን ከፍ ባለ ስኬት ላይ ይገኛል። 


 

የተገኘው ጅምር ውጤትም፤ ኢትዮጵያ የምግብ እርዳታ ከመቀበል ወጥታ ራሷን መመገብ የምትችል ሀገር የማድረግ ታላቁ ህልማችን እውን የሚሆንበት መንገድ ላይ ስለመሆኑ አመላካች ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም