ቀጥታ፡

ሪያል ሶሲዬዳድ የኮፓ ዴል ሬይ ዋንጫን ለአራተኛ ጊዜ አነሳ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በስፔን የኮፓ ዴል ሬይ የፍጻሜ ጨዋታ ሪያል ሶሲዬዳድ አትሌቲኮ ማድሪድን በመለያ ምት አሸንፏል።

በሲቪያ ላ ካርቱጃ ስታዲየም በተካሄደው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በ90 ደቂቃ አትሌቲኮ ማድሪድ እና ሪያል ሶሲዬዳድ ሁለት አቻ ተለያይተዋል።

 

አዴሞላ ሉክማን እና ጁሊያን አልቫሬዝ ለአትሌቲኮ ማድሪድ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

አንደር ባሬኔትክሲያ በጨዋታ እና ማይክል ኦያርዛባል በፍጹም ቅጣት ምት ለሪያል ሶሲዬዳድ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

 

በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ክለቦቹ አቻ በመለያየታቸው 30 ደቂቃ ተጨምሯል።

በጭማሪ ሰዓት ግብ ባለመቆጠሩ ጨዋታው ወደ መለያ ምት አምርቷል።

ሪያል ሶሲዬዳድ በመለያ ምት 4 ለ 3 በማሸነፍ የስፔን ኮፓ ዴል ሬይን (የንጉሱ ዋንጫ) ለአራተኛ ጊዜ አንስቷል።
 

የባስኩ ክለብ ከአምስት ዓመታት በኋላ የውድድሩ አሸንፏል።

አትሌቲኮ ማድሪድ ከ13 ዓመታት በኋላ የኮፓ ዴል ሬይን ዋንጫ የማንሳት ህልሙ አልተሳካም።

የማድሪዱ ክለብ 10 ጊዜ ውድድሩን አሸንፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም