ማንችስተር ዩናይትድ ወሳኝ ድል ተቀዳጅቷል - ኢዜአ አማርኛ
ማንችስተር ዩናይትድ ወሳኝ ድል ተቀዳጅቷል
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2018 (ኢዜአ)፡- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 33ኛ ሳምንት ማንችስተር ዩናይትድ ቼልሲን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ማትያስ ኩንሃ በ43ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።
ባለሜዳው ቼልሲ በርካታ የግብ እድሎችን ቢፈጥርም መጠቀም አልቻለም።
በሁለት አጋማሽ የግብ ቋሚ እና አግጣሚ የገጨባቸው አጋጣሚዎች ተጠቃሽ ናቸው።
ዩናይትድ በጨዋታው ያገኘውን ግልጽ የግብ እድል በመጠቀም አሸንፏል።
በሊጉ 16ኛ ድሉን ያስመዘገበው ማንችስተር ዩናይትድ በ58 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።
ዩናይትድ በሻምፒዮንስ ሊጉ የመሳተፉ ነገር እውን ሊሆን ተቃርቧል።
በውድድር ዓመቱ 11ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ቼልሲ በ48 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ቡድኑ ባለፉት አራት የሊግ ጨዋታዎች ተሸንፏል።
የዛሬው ሽንፈት ቼልሲ በሻምፒዮንስ ሊጉ የመሳተፍ እድሉን ይበልጥ የጠበበ አድርጎታል።
በጨዋታው ለግቡ መቆጠር ምክንያት የሆነው ብሩኖ ፈርናንዴዝ በሊጉ ለ18ኛ ጊዜ ለጎል የሚሆን ኳስ አመቻችቶ አቀብሏል።