ቀጥታ፡

ወራጅ ቀጠና የሚገኘው ቶተንሃም ሆትስፐርስ ከብራይተን ጋር አቻ ተለያየ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 10 /2018 (ኢዜአ)፦  በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 33ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቶተንሃም ሆትስፐርስ  እና ብራይተን  ሁለት አቻ ተለያይተዋል።

ማምሻውን በቶተንሃም ሆትስፐርስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፔድሮ ፖሮ እና ዣቪ ሲመንስ ጎሎቹን ለስፐርስ አስቆጥረዋል።

ካሩ ሚቶማ እና ጆርጂኒዮ ሩተር ለብራይተን ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ባለሜዳው ቶተንሃም አሸነፈ ተብሎ ሲጠበቅ ጆርጂኒዮ ሩተር በ95ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠረው ጎል ብራይተንን አቻ አድርጓል።

የቶተንሃሙ ተከላካይ ኬቨን ዳንሶ የሰራው ስህተት ለሩተር ጎል መቆጠር ምክንያት ሆኗል።

የሩተር ጎል ለቶተንሃም ተጫዋቾች እና ደጋፊዎች ቅስም ሰባሪ ሆኗል።

ቶተንሃም ሆትስፐርስ በ31 ነጥብ ደረጃውን 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ቡድኑ ባለፉት 15 የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም።

ብራይተን በ47 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም