ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከወራጅ ቀጠና የወጣበት ወሳኝ ድል አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከወራጅ ቀጠና የወጣበት ወሳኝ ድል አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 10/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 2 ለ 0 አሸንፏል።
ማምሻውን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ነፃነት ገብረመድህን በ38ኛው እና ፍሬው ሰለሞን በ93ኛው ደቂቃ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ከሶስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ32 ነጥብ ደረጃውን ከ18ኛ ወደ 14ኛ ከፍ በማድረግ ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል።
በሊጉ ሰባተኛ ድሉንም አስመዝግቧል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 10ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ34 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል።
ዛሬ ቀን ላይ በተካሄደ የ28ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ መቀሌ 70 እንደርታ ፋሲል ከነማን 3 ለ 0 አሸንፏል።