ቀጥታ፡

የዓለም አትሌቲክስ አዲስ አበባ የ2027ቱን የግራንድ ፕሪክስ ውድድር በወርቅ ደረጃ እንድታዘጋጅ ወሰነ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 10/2018 (ኢዜአ)፦ አዲስ አበባ የ2027ቱን የዓለም አትሌቲክስ የግራንድ ፕሪክስ ውድድር በወርቅ ደረጃ እንድታዘጋጅ ተመርጣለች።

የዓለም አትሌቲክስ የአንድ ቀን ውድድር የአዲስ አበባ ግራንድ ፕሪክስ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ስታዲየም ዛሬ ተካሄዷል።


 

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ግራንድ ፕሪክስ አጠቃላይ ዝግጅት፣ በመሰረተ ልማቱ ምቹነት፣ በውድድር ሂደቱ እና በደጋፊ የከተማችን ነዋሪ ሞራል እና ስፖርታዊ ጨዋነት በመደመም፤ አዲስ አበባ በሚቀጥለው ዓመት በፈረንጆቹ በ2027 የሚካሄደውን የግራንድ ፕሪክስ ውድድር በወርቅ ደረጃ እንድታዘጋጅ የዓለም አትሌቲክስ በዛሬው መርሐ ግብር ላይ ይፋ ማድረጉን ገልጸዋል።

ከንቲባዋ ውድድሩ በወርቅ ደረጃ እንዲደረግ በመወሰኑ እንኳን ደስ አለን ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም