ቀጥታ፡

ሊድስ ዩናይትድ እና ቦርንማውዝ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 10/2018 (ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ33ኛ ሳምንት ጨዋታዎች መካሄዳቸውን ቀጥለዋል።

በኢላንድ ሮድ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሊድስ ዩናይትድ ዎልቭስን 3 ለ 0 አሸንፏል።

ኖሃ ኦካፎር እና ጀምስ ጀስቲን በጨዋታ፣ ዶምኒክ ካልቨርት-ሉዊን በፍጹም ቅጣት ምት ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

በሊጉ ዘጠነኛ ድሉን ያስመዘገበው ሊድስ ዩናይትድ በ39 ነጥብ 15ኛ ደረጃን ይዟል።

ላለመውረድ በሚያደርገው ፉክክር ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 22ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ዎልቭስ በ17 ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃን ይዟል።

ዎልቭስ በ34ኛ ሳምንት በቶተንሃም ሆትስፐርስ ከተሸነፈ ከሊጉ መወረዱ ይረጋገጣል።

 

በሌላኛው መርሐ ግብር ቦርንማውዝ ኒውካስትል ዩናይትድን 2 ለ 1 አሸንፏል።

በሴንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው ጨዋታ ማርከስ ታቫርኒየር እና አድሪያን ትሩፌርት የማሸነፊያ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

በሊጉ 11ኛ ድሉን ያስመዘገበው ቦርንማውዝ በ48 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት 13 የሊግ ጨዋታዎች አልተሸነፈም።

በውድድር ዓመቱ 15ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኒውካስትል ዩናይትድ በ42 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ቶተንሃም ሆትስፐርስ ከብራይተን፣ ቼልሲ ከማንችስተር ዩናይትድ ምሽት አራት ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም