ቀጥታ፡

አዲስ አበባ ታሪካዊውን የአትሌቲክስ ውድድር በማዘጋጀቷ ክብር ይሰማናል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 10/2018 (ኢዜአ)፦ አዲስ አበባ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የዓለም አትሌቲክስ ውድድር በማዘጋጀቷ ክብር እና ኩራት ይሰማናል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አበቤ የዓለም አዲስ አበባ ግራንድ ፕሪ የአትሌቲክስ ውድድርን በይፋ አስጀምረዋል።


 

ከንቲባዋ ንግግራቸው አዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ውድድር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በማዘጋጀቷ ክብር ይሰማናል ሲሉ ተናግረዋል።

አያይዘውም ውድድሩ በመዲናችን መካሄዱ ከተማችን የስህበት ማዕከል እየሆነች መምጣቷን ያሳያል ብለዋል።

ይህ ሁነት ከውድድር በተሻገረ መልኩ የመግባባት እና አብሮ የመቆም ተምሳሌት መሆኑን ከንቲባዋ አመልክተዋል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ በበኩላቸው፣ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ታላላቅ መድረኮችን በሀገራችን ማዘጋጀት መቻላችን መንግስት ለስፖርት የሰጠውን ትኩረት ያሳያል ብለዋል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲህ አይነት ታላቅ የውድድር መድረክ በማዘጋጀታችን እንደ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ብቻ ሳይሆን እንደ አትሌት ትልቅ ኩራት ተሰምቶኛል ሲሉ መግለጹን የፌዴሬሽኑ መረጃ ያመለክታል።


 

በውድድሩ ይፋዊ የመክፈቻ ስነስርዓት ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማህበራዊ ልማት እና ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ወርቅሰሙ ማሞ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች፣ የኢትዮጵያ ታላላቅ አትሌቶች እና ከተለያዩ ሀገራት የተገኙ እንግዶች ታድመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም