ቀጥታ፡

አትሌት ፋንታዬ አዳነ የ10 ሺህ ሜትር የሴቶች ውድድርን አሸነፈች

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 10/2018 (ኢዜአ)፦ በ10 ሺህ ሜትር የአዲስ አበባ ግራንድ ፕሪክስ ውድድርን አትሌት ፋንታዬ አዳነ በበላይነት አጠናቅቃለች።

የአለም አትሌትክስ የአዲስ አበባ ግራንድ ፕሪክስ የአንድ ቀን ውድድር በአዲስ አበባ ስታዲየም እየተካሄደ ነው።

በዚህ ውድድር ፋንታዬ አዳነ የ10 ሺህ ሜትር የሴቶች ፍጻሜ ውድድርን በአንደኝነት አጠናቃለች።

አትሌት አልማዝ ባራኪ አትሌት ጥበብ እንየው ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሆነው አጠናቀዋል።


 

በተያያዘም በወንዶች የ10 ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር ይስማው ድሉ አንደኛ በመውጣት አሸንፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም