የዓለም አትሌቲክስ የአንድ ቀን ውድድር መካሄድ ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
የዓለም አትሌቲክስ የአንድ ቀን ውድድር መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 10 /2018 (ኢዜአ)፡- የዓለም አትሌቲክስ የአዲስ አበባ ግራንድ ፕሪክስ የአንድ ቀን ውድድር በአዲስ አበባ ስታዲየም መካሄድ ጀምሯል።
ውድድሩ የኢትዮጵያ አትሌቶች ብቻ የሚሳተፉበት እና ዓለም አቀፍ አትሌቶች የሚሳተፉበት በሚል ለሁለት ተከፍሏል።
ታሪካዊው ውድድር በሴቶች የ10 ሺህ ሜትር ፍጻሜ ተጀምሯል።
በውድድሩ ላይ አፍሪካ፣ አውሮፓ፣ እስያ እና ሰሜን አሜሪካን ጨምሮ ከተለያዩ አህጉራት የተወጣጡ ከ70 በላይ አትሌቶች ይሳተፋሉ።
አሜሪካዊቷ ጋቢ ቶማስ እና ኬንያዊው ፈርዲናንድ ኦማኒያላ በውድድሩ ላይ ከሚሳተፉ ታዋቂ አትሌቶች መካከል ይጠቀሳሉ።
ውድድሩ በተለያዩ ርቀቶች ይካሄዳል።
የአዲስ አበባ ግራንድ ፕሪ የዓለም አትሌቲክስ የነሀስ ደረጃ የተሰጠው ነው።
ውድድሩ ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ አትሌቶች የሚሳተፉበት ከመሆኑ ባሻገር አሸናፊ የሚሆኑ አትሌቶች ከፍተኛ ሽልማት እንደሚያገኙ የዓለም አትሌቲክስ አስታውቋል።
የአንድ ቀን ውድድሩ የዓለም አትሌቲክስ ዓመታዊ የኢንተኮንቲነንታል ውድድር አካል ነው።