ህድአት ካሡ ከፓራጓይዋ አሊሰን ባሬሮ ጋር የአውሮፓ ወዳጅነት ዋንጫን በጋራ ከፍተኛ ግብ አግቢነት አጠናቀቀች - ኢዜአ አማርኛ
ህድአት ካሡ ከፓራጓይዋ አሊሰን ባሬሮ ጋር የአውሮፓ ወዳጅነት ዋንጫን በጋራ ከፍተኛ ግብ አግቢነት አጠናቀቀች
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 9/2018 (ኢዜአ)፦ በቱርክዬ አስተናጋጅነት ከመጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ በተካሄደው የዩኤፋ (UEFA) ከ18 ዓመት በታች ሴቶች የወዳኝነት ዋንጫ ዛሬ ተጠናቋል።
በውድድሩ ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አራተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
በውድድሩ ማጠቃለያ ላይ የደቡብ አሜሪካዋ ተወካይ ፓራጓይ የወርቅ ሜዳሊያና የዋንጫ ባለቤት በመሆን ቀዳሚውን ደረጃ ስትይዝ፤ ኖርዌይ ሁለተኛ እንዲሁም አስተናጋጇ ቱርክዬ ሦስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
ኢትዮጵያ በበኩሏ ውድድሩን በአራተኛነት በማጠናቀቋ ለብሔራዊ ቡድኑ የተሳትፎ ሜዳሊያ ተበርክቶለታል።
በግል ብቃት ረገድ ኢትዮጵያዊቷ ተጫዋች ህድአት ካሡ ደምቃ የታየች ሲሆን፤ በውድድሩ ወቅት አራትግቦችን በማስቆጠር ከፓራጓይዋ አሊሰን ባሬሮ ጋር በእኩልነት የውድድሩ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን ማጠናቀቋን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
በተጨማሪም የውድድሩ ኮከብ ተሸላሚዎች ይፋ ሲሆኑ፤ ፓራጓይ ከዋንጫ አሸናፊነቷ ጎን ለጎን የግል ሽልማቶችንም ጠቅልላለች።
በዚህም ታማራ አማሪላ የውድድሩ ኮከብ ግብ ጠባቂ ተብላ ስትመረጥ፤ ሲናትሂያ ካስኮ ደግሞ የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች በመሆን ተሸልማለች።