ኢትዮጵያ በአውሮፓ ወዳጅነት ዋንጫ አራተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ በአውሮፓ ወዳጅነት ዋንጫ አራተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 9/2018 (ኢዜአ):- የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበር ያዘጋጀው የ"UEFA Frendship Cup" ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ውድድር የማጠቃለያ ጨዋታዎች በመካሄድ ላይ ይገኛሉ።
የኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ለደረጃ ባደረገው ጨዋታ በቱርኪዬ 3 ለ 1 ተሸንፏል።
ምትኬ ብርሃኑ ለኢትዮጵያ ብቸኛውን ጎል አስቆጥራለች።
ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ አራተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። ቱርኪዬ ሶስተኛ ደረጃን ይዛለች።
በቻለው ለሜቻ የሚመራው የኢትዮጵያ ከ18 ዓመት ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በውድድሩ ላይ ባደረጋቸው አራት ጨዋታዎች ሁለቱን ሲያሸንፍ በተመሳሳይ በሁለቱ ሽንፈት አስተናግዷል።