የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የቀሪ ሳምንታት መርሐ ግብር ይፋ ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የቀሪ ሳምንታት መርሐ ግብር ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 9/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር የ2018 የውድድር ዘመን መጠናቀቂያ የሆኑትን ከ29ኛ እስከ 38ኛ ሳምንት ያሉ የጨዋታ መርሐ ግብሮችን ይፋ አድርጓል።
እንደ አክሲዮን ማህበሩ መግለጫ ከሆነ፣ የሊጉ ውድድር የሚቀጥለው የኢትዮጵያ ዋንጫ ጨዋታዎች ከተከናወኑ በኋላ ሲሆን፣ ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ዳግም እንደሚጀመር ታውቋል።
ይህ የቀሪ አሥር ሳምንታት መርሃ ግብር የሊጉን ሙሉ የውድድር ጉዞ የሚያጠቃልል ነው።
የቀሩት ሳምንታት ጨዋታዎች በሁለት የሀገሪቱ ስታዲየሞች እንደሚከናወኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ጨዋታዎቹም በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየምና በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳሉ።
የኢትዮጵያ ዋንጫ የጨዋታ ሁኔታን ታሳቢ በማድረግ የ33ኛ እና የ34ኛ ሳምንት መርሃ ግብሮች ላይ ማሻሻያ ሊደረግ እንደሚችል ማህበሩ አመልክቷል።
በተጨማሪም፣ የውድድር ዘመኑ ማጠቃለያ የሆኑት የ37ኛ እና የ38ኛ ሳምንት ጨዋታዎች የክለቦችን የደረጃ እና የውጤት ፉክክር መሰረት በማድረግ ለውጥ ሊደረግባቸው እንደሚችልም ተገልጿል።