መምረጥ ህገ መንግስታዊ መብት መሆኑን በመገንዘብ የምርጫ ካርድ ቀድመን አውጥተናል - አርሶ አደሮች - ኢዜአ አማርኛ
መምረጥ ህገ መንግስታዊ መብት መሆኑን በመገንዘብ የምርጫ ካርድ ቀድመን አውጥተናል - አርሶ አደሮች
ደብረ ብርሃን ፤ ሚያዝያ 9/2018 (ኢዜአ)፦ መምረጥ ህገ መንግስታዊ መብትና የዜግነት ግዴታ መሆኑን በመገንዘብ የምርጫ ካርድ ቀድመን አውጥተናል ሲሉ በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የሚገኙ አርሶ አደሮች ገለጹ።
አርሶ አደሮቹ ለኢዜአ እንዳሉት፤ መምረጥ ህገ መንግስታዊ መብትና የዜግነት ግዴታ መሆኑን በመገንዘብ የምርጫ ካርድ ቀድመው አውጥተዋል።
አርሶ አደር ግዛው መኩሪያ በምርጫ መሳተፍ በህገ መንግስቱ የተሰጠንን ዴሞክራሲያዊ መብት የመጠቀም ዕድል ማግኘት ማለት ነው ብለዋል።
በዚህም ሰላምና ልማትን ያረጋግጣል የሚሉትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ የሚያስችላቸውን የምርጫ ካርድ ቀድመው መውሰዳቸውን ገልጸዋል።
እስካሁን የመራጭነት ካርድ ያልወሰዱ የአካባቢው ነዋሪዎች ከምርጫ ቦርድ የተሰጠውን ተጨማሪ ቀን በመጠቀም ካርዱን እንዲያወስዱም መክረዋል።
ሌላው የከተማዋ ነዋሪ አርሶ አደር ተፈሪ ጌታቸው በበኩላቸው መምረጥ ህገ መንግስታዊ መብትና የዜግነት ግዴታ መሆኑን በመገንዘብ የምርጫ ካርድ ቀድመን አውጥተናል ብለዋል።
በካርዳቸው ለሀገር ልማት ሰላምና እድገት ይጠቅማል የሚሉትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ እለቱን እየተጠባበቁ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
አቶ አርጋው ዘለቀ በበኩላቸው ምርጫ የህዝብ የስልጣን ባለቤትነት ማረጋገጫና የስልጣኔ መገለጫ መሆኑን በመገንዘብ ካርድ ማውጣታቸውን ገልጸዋል።
ምርጫው ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የድርሻችንን እንወጣለን ያሉት ደግሞ አርሶ አደር ደረጀ መሰለ ናቸው።
በምርጫው በቀጣይ አምስት ዓመት ያስተዳድረኛል፤ ይበጀኛል ብለው ያመኑትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ የሚያስችል የመራጭነት ካርድ አውጥተው እለቱን እየተጠባበቁ መሆኑም ገልጸዋል።