ቀጥታ፡

በመደመር እሳቤ ገዥና አሰባሳቢ ትርክቶችን በመገንባት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት መጠናከር በልዩ ትኩረት እየተሰራ ነው

አሶሳ፤ሚያዚያ 8/2018 (ኢዜአ)፦በመደመር እሳቤ ገዥና አሰባሳቢ ትርክቶችን በመገንባት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት መጠናከር በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሐሰን ገለጹ።

7ኛው ሃገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ " ሰላምን ይበልጥ ለማስፋት እና ለማስረጽ የሃይማኖቶች ሚና" በሚል ሃሳብ በአሶሳ ከተማ ተካሂዷል።


 

በመድረኩም የተለያዩ የኃይማኖት አባቶች፣ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ ምሁራንና እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተግኝተዋል።

በመድረኩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሐሰን፤ በመደመር እሳቤ ገዥና አሰባሳቢ ትርክቶችን በመገንባት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት መጠናከር በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ሀገራዊ ምክክርን የዘላቂ የሰላም መፍትሄ በማድረግ በሁሉም አካባቢዎች ጠንካራ ጥረት መኖሩን አንስተው፥ በዚህ ሂደት ውስጥ የሃይማኖት ተቋማት የማይተካ ሚና እንዳላቸውም ተናግረዋል።

በክልሉ የተገኘውን ሰላም በዘላቂነት ለማስቀጠል ከኃይማኖት አባቶች እና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።


 

የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በመንቀሳቀስ በሰላም እና አብሮነት ዙሪያ ሰፊ ግንዛቤ እየፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሰላም ግንባታና አብሮነትን ይበልጥ ለማጠናከር እያደረገ ያለው ጥረት ውጤት እያመጣ መሆኑን አንስተው የሚደረገውን ጥረትም አድንቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም