በያዝነው ወር ሶስት ዓለም አቀፍ ስፖርታዊ ኩነቶች አዲስ አበባ ይካሄዳሉ - ኢዜአ አማርኛ
በያዝነው ወር ሶስት ዓለም አቀፍ ስፖርታዊ ኩነቶች አዲስ አበባ ይካሄዳሉ
አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 8/2018(ኢዜአ)፦ዓለም አቀፉ አዲስ አበባ ግራንድ ፕሪ የአትሌቲክስ ውድድርን ጨምሮ አዲስ አበባ ውስጥ በሚያዚያ ወር ሶስት ዓለም አቀፍ ስፖርታዊ ኩነቶች ይካሄዳሉ።
ከሚካሄዱት ዓለምአቀፍ ስፖርታዊ ኩነቶች ውስጥ አንዱ የአዲስ አበባ ግራንድ ፕሪ የአንድ ቀን የአትሌቲክስ ውድድር በመጪው ቅዳሜ ይካሄዳል።
ይህ ውድድር በአዲስ አበባ ሲካሄድ የመጀመሪያው ሲሆን መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ትኩረት የስፖርት መሰረተ ልማቶች መስፋፋት ምቹ ሆኔታ መፍጠሩ ነው የተገለፀው።
በአዲስ አበባ ስታዲዮም በሚካሄደው ውድድር ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ እና ብዙ ተከታይ ያላቸው አትሌቶች ይሳተፉበታል ተብሏል።
ሲቲ ማውንቴን ባይክ ኢሊሚኔተር ዓለም አቀፍ የብስክሌት ውድድር እና ግራንድ ኢትዮጵያን ረን ሚያዝያ ውስጥ የሚካሄዱ ውድድሮች ናቸው።
ከተማ አስተዳደሩ ውድድሩን ለማሳካት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቂ ዝግጅቶች ከማድረግ በዘለለ በኢትዮጵያ ያሉትን የስፖርት መሰረተ ልማቶች ለማስተዋወቅ የሚያስችሉ ሥራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ተመልክቷል።