ባየር ሙኒክ እና አርሰናል ለግማሽ ፍጻሜ አለፉ - ኢዜአ አማርኛ
ባየር ሙኒክ እና አርሰናል ለግማሽ ፍጻሜ አለፉ
አዲስን አበባ፤ ሚያዝያ 7/2018 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ቀሪ ሁለት የሩብ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታዎች ማምሻውን ተደርገዋል።
በአሊያንዝ አሬና ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ በመደበኛው ክፍለ ጊዜ ባየር ሙኒክ ሪያል ማድሪድን 4 ለ 3 አሸንፏል።
አሌክሳንደር ፓቭሎቪች፣ ሃሪ ኬን፣ሉዊስ ዲያዝ እና ማይክል ኦሊሴ ለባየር ሙኒክ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።
አርዳ ጉለር ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ኪሊያን ምባፔ ቀሪዋን ጎል ለማድሪድ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ተቀይሮ የገባው ኤድዋርዶ ካማቪንጋ በ86ኛው ደቂቃ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ወጥቷል።
ከቀይ ካርዱ በኋላ ሙኒክ ሁለት ግቦችን አስቆጥሯል።
በጨዋታው ባለሜዳው ባየር ሙኒክ የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ቢወስድም ሪያል ማድሪድ በመልሶ ማጥቃት የተሻሉ የግብ እድሎች ፈጥሯል።
ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ አርዳ ጉለር ዳኛ በመናገሩ በቀይ ካርድ ወጥቷል።
ባየር ሙኒክ በድምር ውጤት 6 ለ 4 በማሸነፍ ለግማሽ ፍጻሜ አልፏል።
በሌላኛው መርሐ ግብር አርሰናል እና ስፖርቲንግ ሊዝበን ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
በኤምሬትስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ በቂ የግብ እድሎች የተፈጠሩበት አልነበረም።
ውጤቱን ተከትሎ አርሰናል በድምር ውጤት 1 ለ ዐ በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል።
ጨዋታዎቹን ተከትሎ የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር ተጠናቋል።
በግማሽ ፍጻሜው ባየር ሙኒክ ከፒኤስጂ የሚያደርጉት ጨዋታ ከወዲሁ በጉጉት ይጠበቃል።
አርሰናል በግማሽ ፍጻሜው ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር ይገናኛል።
የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች በሚያዚያ ወር መጨረሻ ይደረጋሉ።