መቻል ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
መቻል ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ አደረገ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት መርሐ ግብር መቻል ድሬዳዋ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል።
ማምሻውን በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ፤ መሐመድ ኑር ናስር በስድስተኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል ድሬዳዋ መሪ ሆኗል።
ዓለምብርሃን ይግዛው በ15ኛው እና ጋናዊው ኮሊንስ ኮፊ በ40ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፏቸው ግቦች መቻልን አሸናፊ አድርገዋል።
የመቻሉ አማካይ ተጫዋች አብዱልከሪም ወርቁ በመጀመሪያው አጋማሽ ቡድኑ ያገኘውን የፍጹም ቅጣት ምት ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
በሊጉ 11ኛ ድሉን ያስመዘገበው መቻል በ43 ነጥብ ደረጃውን ከስድስተኛ ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ዘጠነኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ድሬዳዋ ከተማ በ32 ነጥብ 14ኛ ደረጃን ይዟል።
ዛሬ ቀን ላይ በተደረጉ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ መድን እና ባህር ዳር ከተማ አንድ አቻ ሲለያዩ፤ ሐዋሳ ከተማ እና ምድረ ገነት ሽሬ ያካሄዱት ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
ጨዋታዎቹን ተከትሎ 27ኛ ሳምንት ተጠናቋል።
የ28ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከሚያዝያ 10 ቀን 2018 ዓ.ም አጀምሮ ይካሄዳል።