ሀላባ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አደገ - ኢዜአ አማርኛ
ሀላባ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አደገ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 7/2018 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የ2018 የውድድር ዘመን ምድብ ለ 20ኛ ሳምንት ወሳኝ ጨዋታ ዛሬ በሀላባ ከተማ እና ደሴ ከተማ መካከል ሀዋሳ ላይ ተካሂዷል።
በጨዋታውም ሀላባ ከተማ ደሴ ከተማን 1 ለ 0 በማሸነፍ ነጥቡን 38 አድርሷል።
ይህም አንድ ጨዋታ እየቀረው በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ 2019 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማደጉን እንዲያረጋግጥ ማስቻሉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የ2018 የውድድር ዘመን በምድብ ሀ መሪ ሆኖ ያጠናቀቀው ጋሞ ጨንቻ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ማደጉ ይታወቃል።
የፌዴሬሽኑ መረጃ እንደሚያመለክተው፤ ሁለት ክለቦች ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲያድጉ አራት ክለቦች ደግሞ ከሊጉ የሚወርዱ ይሆናል።