ሦስተኛው የቅርስ ምርምር ጉባዔ ከሚያዚያ 13 ጀምሮ ይካሄዳል - ኢዜአ አማርኛ
ሦስተኛው የቅርስ ምርምር ጉባዔ ከሚያዚያ 13 ጀምሮ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2018 (ኢዜአ)፦ "የኢትዮጵያ ቅርስ ምርምር በዲጂታል ዘመን" በሚል መሪ ሀሳብ ሦስተኛው የቅርስ ምርምር ጉባዔ ከሚያዚያ 13 እስከ 14 ቀን 2018 እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን አስታወቀ።
የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኤሊያስ ሽኩር ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፤ ጉባዔው" የኢትዮጵያ ቅርስ ምርምር በዲጂታል ዘመን" በሚል መሪ ሃሳብ ይካሄዳል።
የምርምር ጉባዔው በቅርስ ልማት ዘርፍ ያሉ ተግዳሮቶችን መርምሮ መፍትሄ ለመስጠት፣ አዳዲስ እውቀቶችን ለመለዋወጥ እና የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ጠቁመዋል።
በዚህ የምርምር ጉባዔ ላይ 13 አዳዲስ የምርምር ጹሁፎች እንደሚቀርቡ ተናግረው፤ ጉባዔው የሚካሄደው በኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን አዳራሽ መሆኑንም አስታውቀዋል።