ቀጥታ፡

ወሎ የብዝኃነት እና የአብሮነት ተምሳሌት ናት - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ 

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 7/2018 (ኢዜአ)፦ ወሎ የብዝኃ ሃይማኖትና ባህል መገኛ፣ የፍቅርና የአብሮነት ተምሳሌት እንዲሁም የታሪክ ማህደር ናት ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።


 

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ወሎ ኮምቦልቻ መግባታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም፣ እንደ ቦርከና ወንዝ የማይነጥፈው የህዝቡ ገራገርነትና የማይጠገበው ትኅትና፣ እንዲሁም እንደ ጦሳ ተራራ የገዘፈው መስተንግዶና ደማቅ አቀባበል ልባቸውን በሐሴት እንደሞላው ገልጸዋል።


 

በወሎ ኮምቦልቻ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ላደረጉላቸውና አርሂቡ ብለው ለተቀበሏቸው ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር፣ ለክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ ለሃይማኖት አባቶች፣ ለሀገር ሽማግሌዎች እና ለመላው የወሎ ሕዝብ ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Ethiopian News Agency #ኢዜአ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም