ፋሲል ከነማ ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ከፍ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
ፋሲል ከነማ ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ከፍ አደረገ
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 6/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ ወላይታ ድቻን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ማምሻውን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ታምራት እያሱ በ20ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።
ታምራት በሊጉ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ብዛት ዘጠኝ አድርሷል።
ውጤቱን ተከትሎ በሊጉ 10ኛ ድሉን ያስመዘገበው ፋሲል ከነማ በ42 ነጥብ ደረጃውን ከስድስተኛ ወደ ሶስተኛ ከፍ አድርጓል።
በውድድር ዓመቱ ስምንተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ወላይታ ድቻ በ31 ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ዛሬ ቀን ላይ በተደረጉ የ27ኛ ሳምንት ጨዋታዎች የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ አዳማ ከተማን በተመሳሳይ 1 ለ 0 አሸንፈዋል።
ሀድያ ሆሳዕና እና ኢትዮጵያ ቡና ሁለት አቻ ተለያይተዋል።