ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 6/2018 (ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የላይቤሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ ከሁለትዮሽ ስብሰባቸው ቀጥሎ ሁለት የመግባቢያ ስምምነቶች ልውውጥ ላይ ተገኝተዋል።
እነዚህ ስምምነቶች በትምህርት፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ በማተኮር ለወደፊት ትብብራችን እንደ ስትራቴጂካዊ መሠረት እና ተግባራዊ ፍኖተ-ካርታ እንደሚያገለግሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።
የትብብር ማዕቀፉ፤ ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያን በመደመር መርህ በማጣመር ለአኅጉራዊ ትስስር ዋነኛ አንቀሳቃሽ ኃይል ከመሆኑም ባለፈ፣ የአፍሪካ ሀገራት በእውነተኛ ትብብር ምን ሊያሳኩ እንደሚችሉ እንደ ታላቅ ተምሳሌት የሚጠቀስ መሆኑም ተገልጿል።