ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከላይቤሪያው ፕሬዝደንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከላይቤሪያው ፕሬዝደንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 6/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከላይቤሪያ አቻቸው ፕሬዝደንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመልዕክታቸው ከላይቤሪያው ፕሬዝዳንት ጋር የነበራቸው ውይይት ፍሬያማ እንደነበር አመልክተዋል።
በውይይታቸው በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን የቆየ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከርና ለማስፋት ወሳኝ ምዕራፍ መከፈቱን ገልጸዋል።
ከሁለትዮሽ ስብሰባው በመቀጠል፣ በሁለቱ ሀገራት በኩል ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ለማሳካት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጡ የመግባቢያ ስምምነቶች መፈረሙን ጠቁመዋል።
እነዚህ ስምምነቶች ኢትዮጵያ በፈጣን የለውጥ ጉዞ ያካበተችውን ልምድ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ለማካፈል እንደ ወሳኝ መሠረት ያገለግላሉ ብለዋል።
በተጨማሪም ስምምነቶቹ ከአጋሮች የተለያዩ ዕይታዎችን በመቅሰም ለአኅጉሩ ዕድገት ዘላቂና አፍሪካዊ መፍትሄዎችን በጋራ ለማፍለቅ እንደ ወሳኝ መሰረት እንደሚያገለግሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው አስታውቀዋል።