የኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለፍጻሜ ሳይደርስ ቀረ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለፍጻሜ ሳይደርስ ቀረ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 6/2018 (ኢዜአ)፦ በ"UEFA Frendship Cup" ከ18 ዓመት በታች ሴቶች መርሐ ግብር ኖርዌይ ኢትዮጵያን 1 ለ 0 አሸንፋለች።
የሁለቱ ሀገራት የምድብ ሁለት ጨዋታ በቱርኪዬ ሪቫ ስታዲየም ተደርጓል።
ውጤቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በስድስት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ለፍጻሜ ማለፍ ሳይችል ቀርቷል።
ኖርዌይ በዘጠኝ ነጥብ ለፍጻሜ አልፋለች።
በተያያዘም በምድብ አንድ በተደረጉ ጨዋታዎች ፓራጓይ ኡዝቤኪስታንነ 7 ለ 0 ስትረታ፣ ቱርኪዬ ሞሮኮን በመለያ ምት አሸንፋለች።
ፓራጓይ በስድስት ነጥብ ተመሳሳይ ነጥብ ያላትን ቱርኪዬ በግብ ክፍያ በልጣ ለፍጻሜ አልፋለች።
ኖርዌይ ከፓራጓይ የፍጻሜው ጨዋታቸውን ሚያዚያ 9 ቀን 2018 ዓ.ም በሪቫ ስታዲየም ያደርጋሉ።
ኢትዮጵያ ሶስተኛ ደረጃን ለማግኘት ከቱርኪዬ ጋር በዕለቱ ትፋለማለች።
የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ያዘጋጀው የወዳጅነት ዋንጫ ከውድድር ባለፈ የክፍለ አህጉራዊ እግር ኳስ ልማት ትብብርን ማጠናከርን ያለመ ነው።