ሀድያ ሆሳዕና እና ኢትዮጵያ ቡና ነጥብ ተጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
ሀድያ ሆሳዕና እና ኢትዮጵያ ቡና ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 6/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 27ኛ ሳምንት መርሀግብር ሀድያ ሆሳዕና እና ኢትዮጵያ ቡና ሁለት አቻ ተለያይተዋል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ እዮብ አለማየሁ እና ብሩክ በየነ የሀድያ ሆሳዕናን ግቦች አስቆጥረዋል።
ዘላለም አባተ እና ራምኬል ጀምስ ለኢትዮጵያ ቡና ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
በጨዋታው ላይ ኢትዮጵያ ቡና ሁለት ጊዜ ቢመራም ውጤቱን ማስጠበቅ አልቻለም።
ሀድያ ሆሳዕና በ33 ነጥብ ደረጃውን ከ13ኛ ወደ 11ኛ ከፍ አድርጓል።
አንድ ተስተካካይ ጨዋታ የሚቀረው ኢትዮጵያ ቡና በበኩሉ በ37 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።