ቀጥታ፡

ሲዳማ ቡና መሪነቱን ያጠናከረበት ድል ተቀዳጀ 

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 6/2018 (ኢዜአ)፦  በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 1 ለ 0 አሸንፏል።

በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አቤል ያለው በመጀመሪያው አጋማሽ ማብቂያ ላይ የማሸነፊያውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ውጤቱን ተከትሎ ሲዳማ ቡና ነጥቡን ወደ 51 ከፍ በማድረግ መሪነቱን አጠናክሯል። ከተከታዩ ነገሌ አርሲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ስምንት ከፍ አድርጓል።

ቡድኑ በአጠቃላይ በውድድር ዓመቱ ያሸነፋቸው ጨዋታዎች ብዛት 14 ደርሰዋል። 

በሊጉ 10ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ34 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም