ኢትዮ ኤሌክትሪክ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮ ኤሌክትሪክ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 6/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ አዳማ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ያሬድ የማነ በ43ኛው ደቂቃ ግቧን አስቆጥሯል።
ከሁለት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ41 ነጥብ ደረጃውን ከስድስተኛ ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል።
በውድድር ዓመቱ ያሸነፋቸውን የጨዋታዎች ብዛት ወደ 10 አድርሷል።
በአንጻሩ በሊጉ ስምንተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዳማ ከተማ በ33 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ቡድኑ ባለፉት ሰባት የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም።