ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በዩኤፋ ወዳኝነት ዋንጫ ለፍጻሜ ለማለፍ ከኖርዌይ ጋር ዛሬ የምታደርገው ጨዋታ ተጠባቂ ነው

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበር ያዘጋጀው የ"UEFA Frendship Cup" ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ውድድር በቱርክዬ በመካሄድ ላይ ይገኛል። 

በውድድሩ ላይ ተሳታፊ የሆነው የኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የምድብ ሁለት የመጨረሻ ጨዋታውን ከኖርዌይ ጋር ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ከ30 ላይ ያደርጋል። 

በቻለው ለሜቻ የሚመራው ብሔራዊ ቡድኑ በምድቡ ባደረጋቸው ጨዋታዎች ዩራጓይን 3 ለ 0፣ ኮስታሪካን 1 ለ 0 አሸንፏል።

ቡድኑ በስድስት ነጥብ እና በአራት የግብ ክፍያ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። 

ተጋጣሚዋ ኖርዌይ በምድቡ ዩራጓይን 6 ለ 0 እና ኮስታሪካን 4 ለ 1 አሸንፋለች።

ኖርዌይ በስድስት ነጥብ እና በዘጠኝ የግብ ክፍያ ምድቡን እየመራች ነው። 

ኢትዮጵያ ወደ ፍጻሜው ጨዋታ ለማለፍ የግድ ኖርዌይን ማሸነፍ ይጠበቅባታል።

በአንጻሩ ኖርዌይ ማሸነፍ ወይም አቻ መውጣት ወደ ፍጻሜው ያሳልፋታል። 

ጨዋታው ጠንካራ ፉክክር ይታይበታል ተብሎ ይጠበቃል።  

በውድድሩ ላይ ድንቅ ብቃቷን እያሳየች የምትገኘው ሕድኣት ካሱ አራቱንም የኢትዮጵያ ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፋለች። ኮስታሪካ ላይ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርታለች።

በተያያዘም በምድብ አንድ ቱርክዬ ከሞሮኮ ከቀኑ 10 ሰዓት ከ30 እና ፓራጓይ ከኡዝቤኪስታን ከረፋዱ 5 ሰዓት ከ30 ላይ ይጫወታሉ።

ሞሮኮ ምድቡን በስድስት ነጥብ ትመራለች። ፓራጓይ እና ቱርክዬ በተመሳሳይ ሶስት ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።

ከምድቡ አንደኛ የሚወጣው ሀገር ወደ ፍጻሜው ያልፋል።

የወዳጅነት ዋንጫው ከውድድር ባለፈ የክፍለ አህጉራዊ እግር ኳስ ልማት ትብብርን ማጠናከርን ያለመ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም