ቀጥታ፡

ማንችስተር ዩናይትድ በሊድስ ዩናይትድ ተሸነፈ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 5/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ32ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሊድስ ዩናይትድ ማንችስተር ዩናይትድን 2 ለ 1 አሸንፏል።

ማምሻውን በኦልድትራፎርድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኖሃ ኦካፎር የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥሯል።

ካሲሚሮ ለዩናይትድ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

የማንችስተር ዩናይትዱ ተከላካይ ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ በ56ኛው ደቂቃ ላይ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።

በጨዋታው ሊድስ ከዩናይትድ በተሻለ ግልጽ የግብ እድሎችን ፈጥሯል። በጨዋታው ላይ ጥሩ እንቅስቃሴ አድርጓል።

የቁጥር ብልጫ የተወሰደበት ማንችስተር ዩናይትድ በሁለተኛው አጋማሽ ወደ ጨዋታው ለመመለስ ያደረገው ጥረት አልተሳካም።

ዩናይትድ በጨዋታው ያሳየው ብቃት የሚጠበቀውን ያህል አልነበረም።

በሊጉ ሰባተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ማንችስተር ዩናይትድ በ55 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል።

ሻምፒዮንስ ሊግ ለመግባት የሚፎካከረው ዩናይትድ ከተከታዩ አስቶንቪላ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት የማስፋት እድል አልተሳካም።

ከስድስት የሊጉ ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ሊድስ ዩናይትድ በ39 ነጥብ 15ኛ ደረጃን ይዟል። ላለመውረድ በሚያደርገው ፉክክር ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል። በሊጉም ስምንተኛ ድሉን አሳክቷል።

ሊድስ ከ24 ዓመታት በኋላ ዩናይትድን በሊጉ አሸንፏል።

ጨዋታውን ተከትሎ 32ኛ ሳምንት ተጠናቋል።

የ33ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከሚያዚያ 10 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ ይካሄዳሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም