ቀጥታ፡

የላይቤሪያው ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ ለስራ ጉብኝት ኢትዮጵያ ገቡ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 5/2018 (ኢዜአ)፦  የላይቤሪያው ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ ለስራ ጉብኝት ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል።

የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ የነገ ብሩህ ተስፋ እየተሰራባት ወደ ምትገኘው ምድረቀደምት ኢትዮጵያ እንኳን በሰላም መጡ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደህና መጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም በፕሬዝዳንቱ ቆይታ እጅግ ፍሬያማ ውይይት እንደሚኖራቸው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም