አርባምንጭ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ ተጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
አርባምንጭ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 5/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 27ኛ ሳምንት አርባምንጭ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ሁለት አቻ ተለያይተዋል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ፍፁም ጥላሁን በ29ኛው እና ተገኑ ተሾመ በ36ኛው ደቂቃ ባስቆጠሯቸው ጎሎች ቅዱስ ጊዮርጊስ መሪ ሆኗል።
ናይጄሪያዊው ጄሮም ፍሊፕ በ42ኛው እና ሴኔጋላዊው ማማዱ ሴክ በ97ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፏቸው ግቦች ለአርባምንጭ ከተማ ወሳኝ አንድ ነጥብ አስገኝተዋል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ የ2 ለ 0 ውጤቱን ማስመዝገብ አልቻለም።
ውጤቱን ተከትሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በ32 ነጥብ ደረጃውን ከ15ኛ ወደ 12ኛ ከፍ አድርጓል። ቡድኑ ሶስተኛ ተከታታይ ድሉን ማስመዝገብ አልቻለም።
አርባምንጭ ከተማ በ23 ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ሽንፈት አስተናግዷል።
በሀዋሳ ከተማ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ሜዳ ውሃ በመያዙ፣ በሀዋሳ ከተማ እና በምድረ ገነት ሽሬ መካከል ሊደረግ የነበረው የምሽት 12 ሰዓት ጨዋታ በዳኞች ውሳኔ ሳይካሄድ ቀርቷል።
የሊጉ አክሲዮን ማህበር የመርሐ ግብሩን አዲስ የጨዋታ ቀን እና ቦታ በቀጣይ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።
ዛሬ በተደረጉ የ27ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች መቀሌ 70 እንደርታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2 ለ 1 ሲረታ ሸገር ከተማ እና ነገሌ አርሲ አንድ አቻ ተለያይተዋል።