ቀጥታ፡

በወራጅ ቀጠና የሚገኘው መቀሌ 70 እንደርታ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አገኘ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 5/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት መርሐ ግብር መቀሌ 70 እንደርታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2 ለ 1 አሸንፏል።

በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፍፁም አለሙ እና ኮትዲቯራዊው አብዱላጢፍ ባምባ የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

ግብ አስቆጣሪው ኮትዲቯራዊው አብዱላጢፍ ባምባ በ82ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ወጥቷል። 

ዳዊት ገብሩ ለወልዋሎ ብቸኛውን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ከስድስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው መቀሌ 70 እንደርታ በ26 ነጥብ 19ኛ ደረጃን በመያዝ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ላለመውረድ በሚያደርገው ትግል ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል።

በሊጉ ያስመዘገባቸውን ድሎች ብዛትም ወደ አምስት ከፍ አድርጓል።

በአንጻሩ በሊጉ 10ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ29 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

ወልዋሎ ባለፉት ሶስት የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም