ጋሞ ጨንቻ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አደገ - ኢዜአ አማርኛ
ጋሞ ጨንቻ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አደገ
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 5/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የ2018 የውድድር ዘመን የምድብ ሀ የምድብ ጨዋታዎች ዛሬ ፍፃሜያቸውን አግኝተዋል።
በጅማ ስታዲየም ቡራዩ ክፍለ ከተማን የገጠመው ጋሞ ጨንቻ 3 ለ 0 አሸንፏል።
ክለቡ ይህንን ድል ተከትሎ በድምሩ 41 ነጥቦችን በመያዝ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ማደጉን እንዳረጋገጠ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
ጋሞ ጨንቻ በ2019 ዓ.ም በፕሪሚየር ሊጉ ላይ ይሳተፋል።
ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሚያድገው ቀሪ አንድ ክለብ በቀጣይ ጨዋታዎች የሚለይ ይሆናል።
የፌዴሬሽኑ መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ሁለት ክለቦች ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሲያድጉ አራት ክለቦች ደግሞ ከሊጉ የሚወርዱ ይሆናል።