የሸገር ከተማ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ - ኢዜአ አማርኛ
የሸገር ከተማ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 5/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ሸገር ከተማ እና ነገሌ አርሲ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ከቤ ብዙነህ በ60ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ግብ ነገሌ አርሲ መሪ ሆኗል።
ብዙም ሳይቆይ ዮሴፍ ታረቀኝ በ64ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ጎል ሸገር ከተማን አቻ አድርጓል።
ውጤቱን ተከትሎ ሸገር ከተማ በ32 ነጥብ ደረጃውን ከ14ኛ ወደ 11ኛ ከፍ አድርጓል።
ነገሌ አርሲ በ43 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል። ከመሪው ሲዳማ ቡና ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት የማጥበብ እድል ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
ሁለቱም ቡድኖች በተመሳሳይ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች አላሸነፉም።
ሸገር ከተማ እና ነገሌ አርሲ ዘንድሮ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ያደጉ ቡድኖች ናቸው።