የመውረድ ስጋት ያንዣበበት ቶተንሃም ሆትስፐርስ በሰንደርላንድ ተሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
የመውረድ ስጋት ያንዣበበት ቶተንሃም ሆትስፐርስ በሰንደርላንድ ተሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 4/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 32ኛ ሳምንት ሰንደርላንድ ቶተንሃም ሆትስፐርስን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በስታዲየም ኦፍ ላይት በተካሄደው ጨዋታ ኖርዲ ሙኪዬል በ61ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።
ውጤቱን ተከትሎ ሰንደርላንድ በ46 ነጥብ 10ኛ ደረጃን ይዟል።
ቶተንሃም ሆትስፐርስ በ30 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
የሰሜን ለንደኑ ክለብ ባለፉት 14 የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም። ቡድኑ ወራጅ ቀጠና ሲገባ ከ17 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
አዲሱ የቶተንሃም አሰልጣኝ ሮበርቶ ዲ ዘርቢ በመጀመሪያ ጨዋታቸው ሽንፈት አስተናግደዋል።
በሌላኛው መርሐ ግብር ኖቲንግሃም ፎረስት እና አስቶንቪላ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
ኒኮ ዊሊያምስ ለፎረስት፣ የኖቲንግሃሙ ሙሪሎ በራሱ ላይ ለአስቶንቪላ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ኖቲንግሃም ፎረስት በ33 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዟል።
አስቶንቪላ በ55 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል። ሻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ በሚያደርገው ፉክክር ወሳኝ ሶስት ነጥብ ብሏል።
ክሪስታል ፓላስ ከመመራት ተነስቶ ኒውካስትል ዩናይትድን 2 ለ 1 አሸንፏል።
ጂን-ፍሊፕ ማቴታ በጨዋታ እና በፍጹም ቅጣት ምት የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥሯል።
ማቴታ በ94ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ጎል ፓላስን አሸናፊ አድርጋለች።
ዊሊያም ኦሱላ ለኒውካስትል ዩናይትድ ግቧን ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ክሪስታል ፓላስ እና ኒውካስትል ዩናይትድ በተመሳሳይ 42 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው 13 እና 14ኛ ደረጃን ይዘዋል።
ምሽት 12 ሰዓት ከ30 ላይ ቼልሲ ከማንችስተር ሲቲ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።