ከ17 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የደቡብ ሱዳን አቻውን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
ከ17 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የደቡብ ሱዳን አቻውን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 4/2018 (ኢዜአ)፦ በ10ኛው የፊፋ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች የዓለም ዋንጫ የአፍሪካ ዞን ቅድመ ማጣሪያ በመጀመሪያ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ደቡብ ሱዳንን 2 ለ 0 አሸንፋለች።
በጁባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቤተልሔም ግዛቸው እና ምኀረት አየለ የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።
ቡድኑ በጨዋታው የተሻለ እንቅስቃሴ አድርጓል።
ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ እድሏን አስፍታለች።
የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ ሚያዚያ 10 ቀን 2018 ዓ.ም በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይካሄዳል።
ኢትዮጵያ በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፈች ሁለተኛው ዙር ጨዋታዋን ከማላዊ እና ብሩንዲ አሸናፊ ጋር ታደርጋለች።
10ኛው የፊፋ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች የዓለም ዋንጫ በሞሮኮ አስተናጋጅነት ከጥቅምት 7 እስከ ጥቅምት 28 ቀን 2019 ዓ.ም ይካሄዳል። 24 ሀገራት በውድድሩ ላይ ይሳተፋሉ።
በማጣሪያ የሚያልፉ አራት የአፍሪካ ሀገራት በሶስት ዙሮች በሚደረጉ ጨዋታዎች ይለያሉ።