የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ - ኢዜአ አማርኛ
የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 4/2018 (ኢዜአ)፦ተቀማጭታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች እና አምባሳደሮች ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ ለትንሳኤ በዓል እንኳን አደረሳችሁ በማለት በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የደስታ እንዲሆን ተመኝቷል።
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ የትንሳኤ በዓልን ለሚያከብሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ልባዊ የመልካም ምኞት መግለጫዬን አስተላልፋለሁ ሲሉ ገልጸዋል።
በጾሙ ወቅት የሚታየው ጽናትና የኢትዮጵያ ውብ እሴቶች፣ የኢትዮጵያውያንን ጥልቅ እምነትና የበለጸገ የባህል ማንነት በግልጽ የሚያሳዩ ናቸው ብለዋል።
የትንሣኤ በዓል የታደሰ ሕይወትን፣ ተስፋንና በረከትን ይዞ እንዲመጣ ተመኝተዋል።
በኢትዮጵያ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ያለው ደግሞ በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ ነው።
በዓሉ የሰላም እና የፍቅር እንዲሆን ተመኝቷል።
በኢትዮጵያ የአውስትራሊያ አምባሳደር ፒተር ሀንተር (ዶ/ር) የትንሳኤ በዓል የደስታ እና የሀሴት እንዲሆን ተመኝተዋል።
በኢትዮጵያ የዩናይትድ ኪንግደም ኤምባሲ የትንሳኤ በዓል የተስፋ፣የእድሳት እና የአብሮነት ጊዜ መሆኑን አመልክቷል።
በዓሉ የሰላም፣የፍቅር እና የደስታ እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል።
በኢትዮጵያ የኢራን ኤምባሲ እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ ሲል የመልካም ምኞት መግለጫውን አስተላልፏል።
በኢትዮጵያ የፓኪስታን ኤምባሲ የትንሳኤ በዓል የደስታ እና የበረከት እንዲሆን ተመኝቷል።
ስዊድን፣ ስዊዘርላንድ፣ ጀርመን፣ አርሜኒያ፣ እና ካናዳ ሌሎች ለትንሳኤ በዓል መልካም ምኞታቸውን ከገለጹ ኤምባሲዎች መካከል ይጠቀሳሉ።
በተያያዘም የተባበሩት መንግግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቢሮ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ሲል መልካም ምኞቱን ገልጿል።
የትንሳኤው ወቅት የተስፋ፣የመታደስና የአብሮነት እንዲሆንም ተመኝቷል።