የትንሳኤ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የትንሳኤ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 4/2018 (ኢዜአ)፡- የትንሳኤ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል።
በዓሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳበት ዕለት የሚታወስበት ነው።
የትንሳኤ በዓልን አስመልክቶ የኃይማኖት አባቶች ባስተላለፉት መልዕክት ሕዝበ ክርስቲያኑ የትንሳኤን በዓል የአንድነትና የቸርነት እሴቶችን በማጎልበት፣ በመረዳዳትና በአብሮነት እንዲያሳልፍ አባታዊ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
ሕዝበ ክርስቲያኑ ከቂም በቀልና ከጥላቻ በመራቅ፣ ከሌሎች ወንድምና እህቶቻቸው ጋር በመተባበር ለሀገር ሰላምና ፍቅር መስራት እንዳለበት አመልክተዋል።
የሃይማኖት አባቶቹ በመልዕክታቸው ማጠቃለያ ላይ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የደስታ እንዲሆን ለሁሉም የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
የትንሳኤ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በተለያዩ ዝግጅቶች በመላው ኢትዮጵያ እየተከበረ ይገኛል።