ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ኮስታሪካን በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍጻሜው አለፈች 

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 3 /2018 (ኢዜአ)፦ በ"UEFA Frendship Cup" ጨዋታ የኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ኮስታሪካን 1 ለ 0 አሸንፏል።

በሪቫ ስታዲየም በተካሄደው የምድብ ሁለት ጨዋታ ህዳአት ካሡ በ37ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥራለች።

ምትኬ ብርሃኑ በጨዋታው በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥታለች።

ኢትዮጵያ የቁጥር ብልጫ ቢወሰድባትም ውጤቷን አስጠብቃ ወጥታለች።

ውጤቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ነጥቡን ወደ ስድስት ከፍ አድርጓል።

በቻለው ለሜቻ የሚመራው ብሔራዊ ቡድን በመጀመሪያው ጨዋታ ኮስታሪካን 3 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።

በዚሁ ምድብ ዛሬ በተደረገው ሌላኛው ጨዋታ ኖርዌይ ዩራጓይን 6 ለ 0 በመርታት በተመሳሳይ ስድስት ነጥብ ኢትዮጵያን በግብ ክፍያ በልጣ አንደኛ ደረጃን ይዛለች።

ኢትዮጵያ እና ኖርዌይ ሚያዚያ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት ከ30 የሚያደርጉት ጨዋታ ከወዲሁ ይጠበቃል።

የምድቡ ቀዳሚ የሚሆነው ሀገር የዋንጫ ተፋላሚነቱን እንደሚያረጋግጥ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመለክታል።

በውድድሩ ላይ ስምንት ሀገራት እየተሳተፉ ነው።

የወዳጅነት ዋንጫው ከውድድር ባለፈ የክፍለ አህጉራዊ እግር ኳስ ልማት ትብብርን ማጠናከርን ያለመ ነው። 

የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበር ያዘጋጀው እና በቱርኪዬ እየተካሄደ የሚገኘው  የ"UEFA Frendship Cup" ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ውድድር እስከ ሚያዝያ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም