ቀጥታ፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 3 /2018 (ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈዋል።

ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የትንሣኤ በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሁሉ መዳን ያለውን ፍቅር እስከ መስቀል ሞት የገለጸበትና የሞት ድል የተበሰረበት ታላቅ ዕለት ነው ብለዋል።

በመሆኑም በዓሉን ስናከብር በታላቅ ፍቅር፣ በትሕትና እና በመተሳሰብ ሊሆን ይገባል ነው ያሉት።

ከንቲባዋ በመልዕክታቸው በዓሉ አቅመ ደካሞችን በመርዳት የፍቅር እጃችንን የምንዘረጋበት፣ አንዳችን ለሌላው የደስታ ምንጭ እና የሰላም ተምሳሌት የምንሆንበት የፍቅር በዓል ይሁንልን ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም