ቀጥታ፡

የትናንቶችን ባስታወስን ቁጥር የነገዎችን እናፈራለን - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 3 /2018 (ኢዜአ)፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በዛሬው ዕለት ወደ ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም ዘንድ በመሄድ የእንኳን አደረሰዎ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ልዑሉ ሀገራቸውን በቅንነት ያገለገሉ አንጋፋ አባት መሆናቸውን የጠቀሱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ዛሬም በንቁነታቸውና በአስታዋሽነታቸው ላይ ይገኛሉ ብለዋል።

የትናንቶችን ባስታወስን ቁጥር የነገዎችን እናፈራለን ሲሉም አክለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም