ቀጥታ፡

የሊጉ መሪ አርሰናል በቦርንማውዝ ተሸነፈ 

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 3/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ32ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቦርንማውዝ አርሰናልን 2 ለ 1 አሸንፏል። 

በኤምሬትስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጁኒየር ክሩፒ እና አሌክስ ስኮት የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

ቪክቶር ዮኮሬስ ለአርሰናል ብቸኛውን ግብ በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ ጋር አገናኝቷል።

ጨዋታው ተመጣጣኝ ፉክክር ታይቶበታል።

በውድድር ዓመቱ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው የሊጉ መሪ አርሰናል 70 ነጥብ ላይ ረግቷል። በዋንጫ ፉክክሩ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ጥሏል። 

አርሰናል ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 12 ከፍ የማድረግ እድል ሳይጠቀምበት ቀርቷል።

ከአምስት ተከታታይ የአቻ ውጤቶች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ቦርንማውዝ በ45 ነጥብ በ45 ነጥብ ደረጃውን ከ13ኛ ወደ 9ኛ ከፍ አድርጓል። ቡድኑ ባለፉት 12 የሊግ ጨዋታዎች አልተሸነፈም።

ቦርንማውዝ በሊጉ 10ኛ ድሉን አሳክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም