ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪኤግዚም ባንክ ፕሬዝደንት ዶክተር ጆርጅ ኢሎምቢ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 3/2018 (ኢዜአ):- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪኤግዚም ባንክ ፕሬዝደንት ዶክተር ጆርጅ ኢሎምቢ ጋር ውይይት አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የአፍሪኤግዚም ባንክ ፕሬዝደንት የሆኑትን ዶክተር ጆርጅ ኢሎምቢን ዛሬ መቀበላቸውን ገልጸዋል።

በነበረን የጋራ ቆይታ፣ ስትራቴጂካዊ ግንኙነታችንን በምናጠናክርባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም